Ethiopian Birthday Wishes, Postcards, Messages, Images, Quotes & Text…
Ethiopian Birthday Wishes
የልደት በአልህ በበራሪ ወረቀቶች፤ በብዙ ቀለማት ባጌጡ ፊኛዎች፤ በሚያማምሩ አበባዎች፤ በጥሩ ሰዎች፤ በደስታ እና በሳቅ የተሞላ ያማረ እንዲሆን እመኝልሃ/ሻለው። መልካም ልደት።
ጸሃይዋ እንድትወጣ፤ አበባዎች እንዲፈነድቁ፤ አእዋፋት እንዲዘምሩ አይኖችህ/ሽን ግለጥ። ምክንያቱም ሁሉም ሰው መልካም ልደት ሊልህ/ሽ እና ፊትህ/ሽ ላይ የሚያምር ፈገግታ ለማየት እየጠበቀ ነው። መልካም ልደት።
ይህ መልእክት ሙሉ ለሙሉ ተፈጥሮአዊ የሆነ ከስብ እና ከኮሌስትሮል የጸዳ፤ ነገር ግን ብዙ ስኳር ይገኝበታል። ሆኖም ግን መቼም ቢሆን እንዳንተ/ቺ ጣፋጭ ሊሆን አይችልም። መልካም ልደት።
አንዳንድ ነገሮች ሳይሰሩ፤ አንዳንድ ቃላት ሳይነገሩ፤ አንዳንድ ስሜቶች ሳይገለጹ ይቀራሉ። ነገር ግን እንዳንተ/ቺ አይነት ምርጥ ሰዎች መቼም መልካም ልደት ሳይባሉ አይቀርም። መልካም ልደት።
ዛሬ ልደትህ/ሽ ነው። ዘና በል/ይ፣ ዘፈን ክፈት/ች፣ ደንስ/ሺ ተንቀሳቀሺ፣ ሻማ ለኩስ/ሺ፣ኬክህ/ሽን ቁረስ/ሺ ቀኑን ምርጥ ቀን አድርገ/ጊው። ምክንያቱም ይህ ልዩ ቀን ነው። የልደት ቀንህ/ሽ ነው። መልካም ልደት እመኝልሃ/ሻለው።
እስኪ ወደ ውጭ ተመልከት/ቺ ጸሃይዋ ላንተ ፈንጥቃለች፣ ዛፎቹ እየተወዛወዙ ነው፣አእዋፋት እየዘመሩ ነው ምክንያቱም ለሁሉም መልካም የልደት በአል እንዲመኙልህ ነግሬአችዋለው።
ፈጣሪ አንተ/ቺን ወደ አንተ የሚደርሰውን ወርቃማ የጸሃይ ብርሃን ፍንጣቂ በደስታ፣በስኬት፣በብልጽግና ያሸብርቀው። መልካም ልደት።
ፈጣሪ አንተ/ቺን ወደ ህይወት ስላመጣህ/ሽ ላመሰግነው እወዳለው። እንዲሁም ደግሞ ከዚህ በኋላ ፈጣሪ ብዙ ዘመን እንድትኖር መልካም ፍቃዱ እንዲሆን መልካም ምኞቴ ነው። መልካም ልደት።