
Ethiopian Debre Tabor (Buhe) Holiday 2012 Postcards, Wishes, Messages,…
ቡሄ-በሉ-1.mp3 (350 downloads) The Historical cause of Ethiopian Debre Tabor (Buhe) celebration and Holiday
የዚህ በዓል መሠረት የክርስትና እምነት ሲሆን፣ በግእዝ ደብረ ታቦር የታቦር ተራራ ማለት ነው ፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ጸሃይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።
የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯፦ ቁጥር ፩ እስከ ፭ ” ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያእቆብን ወንድሙንም ዮሃንስንን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሊያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።”
ይህ በአል በየአመቱ ነሃሴ 13 ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል። ይህ በአል በ ‘ቡሄ’ ይባላል።
Why is the Debre Tabor holiday is called and known as BUHE by most ethiopians?
ቡሄ ማለት (መላጣ ገላጣ) ማለት ነው። በሃገራችን የክረምቱ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በዚሁ በአል አከባቢ ስለሆም ይመስላል ‘ቡሄ (መላጣ ገላጣ)’ የሚለው ስያሜ የተሰጠው ።
‘ድርጊቱ በተፈጸመበት በፍልስጤም ግን የደመና መልክ የማይታይበት ፍጹም የበጋ ወራት ነው” በሃገራችን ህጻናቱ ይህ በአል ከመድረሱ በፊት ቀደም አድርገው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ(ሲያናጉ) ይሰነብታሉ። እናቶችም ለዚሁ በአል የሚሆን ዳቦ ለመጋገር (የሚከበረው በዳቦ(ሙልሙል ዳቦ) ነውና) ስንዴአቸውን ሲያጥቡ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ።
በአሉ እንደ ነገ ሲሆን እንደ ዛሬ በዋዜማው (ነሃሴ 12) የሰፈር ህጻናት በየቤቱ እየዞሩ “ቡሄ በሉ! ቡሄ መጣ ያ መላጣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ። እዚህ ለይ ቡሄ ያሉት ዳቦውን ነው። በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሱ ይሰጧቸዋል።ሄደው ዳቦአቸውን እየገመጡ ሲጋረፉ ይውላሉ።
Cracking of the Whip
የጅራፉ መጮህ የድምጸ መለኮት፤ጅራፉ ሲጮህ ማስደንገጡ የሃዋርያትን (ጴጥሮስን፣የያእቆብንና፣ የዮሃንስን) ድምጸ መልኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል።
Bonfires at night
የቡሄ እለት ማታ ችቦ ያበራል። ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው። “ የቡሄ እለት ለዘመድ ለአዝማድ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በልጆቹ ልክ ዳቦ ይሰጣል። በተጨማሪም ለክርስትና ልጅ ለሰጡት ልጅ ለአማች፣ ምራት፣ በቅርብ እውቅያ ላለውም ሁሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶድስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተማሪ ቤት ደሞ ደብረ ታቦር የተማሪዎች በአል ነው። ተማሪዎች ቀደም አርገው (ስለ ደብረ ታቦር) እያሉ እህሉን ጌሾውን ብቅሉን ይለምናሉ፤ ህዝቡም በአሉን ስለሚያውቅ በገፍ ይሰጣቸዋል። የደብረ ታቦር እለት ጠላውን ጠምቀው ቆሎውን ቆልተው ዳቦውን ጋግረው ሊያስቅድሱ የመጡትን ም እ መናን ሁሉ ከቅዳሴ በኋላ ይጋበዛሉ። ይህ እስካሁን በቤተክርስቲያንበትምህርት ቤቶች የሚሰራበት ነባር ትውፊት ነው።
And now Here is a song with a modern twist Hoya-Hoye-_-Assiyo-Bellema-short-version-Westpark-Music-2.mp3 (466 downloads)
Here is a link to download a full version of the song👇👇
https://westparkmusic.bandcamp.com/track/hoya-hoye-assiyo-bellema-short-version
WISH YOU A VERY HAPPY BUHE
sources
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ፣ “የበዓላትና ዓጽዋማት ቀኖና” ፤ http://ethiopianorthodox.org/amharic/abeyetbealat/yebealatenaatsewamat.pdf
https://am.wikipedia.org/wiki/ደብረ_ታቦር_(ዓመት_በዓል)