የኢሬቻ በአል መልካም ምኞት መግለጫ መልክቶች፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ መልክቶች መልክቶች…
Table of Contents
የኢሬቻ በአል
የኢሬቻ በአል በኢትዮጵያ በኦሮሞ ብሄር በገዳ ስርአት ለ ዋቃ (waaqa) ምስጋና ለማቅረብና ጸሎት ለማድረስ የሚከናወን በአል ነው።
የገዳ ስርአት ፍትሃዊ የሆነ ማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ክስተቶችን በፍትሃዊነትና በእኩልነት ለማስተዳደር የሚረዳ የኦሮሞ ብሄር ትልቅ ተቋም ነው።
የገዳ ስርአት በስሩ irreechaa(ኢሬቻ)፣ ateetee(አቴቴ)፣ siiqqee(ሲቄ)፣ guddifachaa(ጉዲፈቻ)፣harmahoosisu (ሃርማሆሲሱ)፣moggaasa(ሞጋሳ)፣ jaarsummaa (ጃርሱማ) ተቋማትን ይይዛል።
የኢሬቻ በአል መከበር ምክንያት?
የኢሬቻ በአል የሚከበረው በ በጋ ውቅት ሲሆን ለሰው ልጅ እና ለሌሎች ፍጥረታት ሁሉ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ለሚያሟላው ዋቃ (ፈጣሪ እንደማለት ነው።) ምስጋናን መግለጫ በአል ነው።
በገዳ ስርአት ዋቃ ሁሉን የፈጠረ የህይወት ምንጭ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። ዋቃ ፍጹም እውነተኛ፣ ንጹህ፣ ሃ ጢያት የሌለበት በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ መገኘት የሚችል ነው።
በኢሬቻ በአል ወቅት የበአሉ ታዳሚዎች ዋቃን ሰላምና መረጋጋት እንዲያሰፍን፣ህግና ማህበራዊ ስርአት እንዲከበር፣ ተፈጥሮን እንዲጠብቅ እና ብልጽግና እና መትረፍረፍ እንዲመጣ ይለምኑታል።
የኢሬቻ በአል የት ይከበራል?
ኢትዮጵያ ውስጥ
የኢሬቻ በአል የሚከበረው በወንዝ ዳርቻ ወይም ደግሞ በተራራ አናት ላይ ነው።
የኢሬቻ በአል በየአመቱ በመስከረም ወር የመስቀል በአልን ተከትሎ በእሁድ ቀን በ ሆራ ሃርሰዲ( hora harsadi) መሬት በቢሾፍቱ ከተማ በድምቀት ይከበራል። ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ በመጋቢት ወር ይከበራል።
የኢሬቻ በአል በዋነኝነት በቢሾፍቱ ከተማ ይከበር እንጂ በሌሎች ቦታዎች ማለትም በ መልካ አቴቴ(malkaa ateetee)(ወደ ቡራዩ ከተማ አካባቢ፣በገፈርሳ ወንዝ ዙሪያ) ፣በቱሉ እንጅሮ(ireechaa tulluu injirroo)(ምስራቅ ወለጋ ) ይከበራል።
የአቴቴ እና ሲቄ ተቋማት በአል
ሰለኢሬቻ በአል ሲወራ የአቴቴ(ateetee) እና የሲቄ(siiqqee) ተቋማት በአል ሳይታወስ አይታለፍም። እነዚህ በአላት በተለይም የሴቶች በአላት ናቸው።
የአቴቴ በአል የወላድነት፣ፍሬ የመስጠት በአል ሲሆን በዚህ በአል በሴቶች የሚመራ የጸሎት፣የምርቃትና የይቅርታ ስነስርአቶች ይከናወናሉ።
አቴቴ በዋነኝነት የሴቶች በአል ሲሆን ከወንዶች ይልቅ ፈጣሪ ለሴቶች ጸሎት በቶሎ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ስለሚታመን በአቴቴ ሴቶች ጸሎታቸውን በተለያየ ጊዜ ለዋቃ ያደርሳሉ።
ሲቄ ደግሞ ሴቶች ጋብቻ በሚፈጽሙበት ጊዜ የሚሰጣቸው በትር ሲሆን ይህም በትር የሴቶችንና የወንዶችን እኩልነት ያሳያል።
የኢሬቻ በአል በ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ ሳይንስ እና ባህላዊ ድርጅት(UNESCO) በማይዳሰሱ ቅርሶች ምድብ የተካተተ በአል ነው።