የ ደብረ ታቦር (ቡሄ) የእንኳን አደረሳቹ (መልካም ምኞት መግለጫ) መልክቶች፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ መልክቶች (SMS)

ቡሄ አልበም 1 የቡሄ የእንኳን አደረሳቹ መልክቶች፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ መልክቶች (SMS.

የ ደብረ ታቦር (ቡሄ) የእንኳን አደረሳቹ (መልካም ምኞት መግለጫ)…

በማህበራዊ ሚዲያ ላይ ይከተሉን
ቡሄ  ደብረታቦር

የዚህ በዓል መሠረት የክርስትና እምነት ሲሆን፣ በግእዝ ደብረ ታቦር የታቦር ተራራ ማለት ነው ፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ጸሃይ  የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።

የማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯፦  ቁጥር ፩ እስከ ፭ ” ከስድስት ቀንም በኋላ ኢየሱስ ጴጥሮስንና ያእቆብን ወንድሙንም ዮሃንስንን ይዞ ወደ ረጅም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። በፊታቸውም ተለወጠ፥ ፊቱም እንደ ፀሐይ በራ፥ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እነሆም፥ ሙሴና ኤሊያስ ከእርሱ ጋር ሲነጋገሩ ታዩአቸው። ጴጥሮስም መልሶ ኢየሱስን ጌታ ሆይ፥ በዚህ መሆን ለእኛ መልካም ነው፤ ብትወድስ፥ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ። እርሱም ገና ሲናገር፥ እነሆ፥ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው፥ እነሆም፥ ከደመናው። በእርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው፤ እርሱን ስሙት የሚል ድምፅ መጣ።”

ይህ በአል በየአመቱ ነሃሴ 13 ቀን በታላቅ ድምቀት  ይከበራል።

የደብረ ታቦር በአል በብዙሃን ዘንድ የሚታወቀው ‘ቡሄ’ የሚባለውን ቅጥያ ስም እንዴት አገኘ ትርጓሜውስ ምንድነው?

ቡሄ ማለት (መላጣ ገላጣ) ማለት ነው። በሃገራችን የክረምቱ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በዚሁ በአል አከባቢ ስለሆም ይመስላል  ‘ቡሄ (መላጣ ገላጣ)’ የሚለው ስያሜ የተሰጠው ።

‘ድርጊቱ በተፈጸመበት በፍልስጤም ግን የደመና መልክ የማይታይበት ፍጹም የበጋ ወራት ነው” በሃገራችን ህጻናቱ ይህ በአል ከመድረሱ በፊት ቀደም አድርገው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ(ሲያናጉ) ይሰነብታሉ። እናቶችም ለዚሁ በአል የሚሆን ዳቦ ለመጋገር (የሚከበረው በዳቦ(ሙልሙል ዳቦ) ነውና) ስንዴአቸውን ሲያጥቡ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ።

በአሉ እንደ ነገ ሲሆን እንደ ዛሬ በዋዜማው (ነሃሴ 12) የሰፈር ህጻናት በየቤቱ እየዞሩ “ቡሄ በሉ! ቡሄ መጣ ያ መላጣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ። እዚህ ለይ ቡሄ ያሉት ዳቦውን ነው። በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሱ ይሰጧቸዋል።ሄደው ዳቦአቸውን እየገመጡ ሲጋረፉ ይውላሉ።

ደብረታቦር ሆያ ሆዬ

ለቡሄ ጅራፍ የሚጮህበት ምክንያት?

የጅራፉ መጮህ የድምጸ መለኮት፤ጅራፉ ሲጮህ ማስደንገጡ የሃዋርያትን (ጴጥሮስን፣የያእቆብንና፣ የዮሃንስን) ድምጸ መልኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል።

ችቦ የሚበራበት ምክንያት?

የቡሄ እለት ማታ ችቦ ያበራል። ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው።  “ የቡሄ እለት ለዘመድ ለአዝማድ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በልጆቹ ልክ ዳቦ ይሰጣል። በተጨማሪም ለክርስትና ልጅ ለሰጡት ልጅ ለአማች፣ ምራት፣ በቅርብ እውቅያ ላለውም ሁሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶድስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተማሪ ቤት ደሞ ደብረ ታቦር የተማሪዎች በአል ነው። ተማሪዎች ቀደም አርገው (ስለ ደብረ ታቦር) እያሉ እህሉን ጌሾውን ብቅሉን ይለምናሉ፤ ህዝቡም በአሉን ስለሚያውቅ በገፍ ይሰጣቸዋል።

የደብረ ታቦር እለት ጠላውን ጠምቀው ቆሎውን ቆልተው ዳቦውን ጋግረው ሊያስቅድሱ የመጡትን ምእመናን ሁሉ ከቅዳሴ በኋላ ይጋበዛሉ። ይህ እስካሁን በቤተክርስቲያን በትምህርት ቤቶች የሚሰራበት ነባር ትውፊት ነው።

እስቲ ደግሞ በአሁኑ ዘመን ያለውን ዘመናዊ የሆያ ሆዬ ሙዚቃ እነሆ

Hoya-Hoye-_-Assiyo-Bellema-short-version-Westpark-Music-2.mp3 (655 downloads )

የዚህን ሙዚቃ ሙሉ ይዘት ለማውረድ ወደዚህ አድራሻ ይሂዱ 👇👇

https://westparkmusic.bandcamp.com/track/hoya-hoye-assiyo-bellema-short-version

መልካም የ ደብረ ታቦር (ቡሄ) በአል ይሁንላችሁ!!

በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQ)

የደብረ ታቦር በአል በብዙሃን ዘንድ የሚታወቀው ‘ቡሄ’ የሚባለውን ቅጥያ ስም እንዴት አገኘ ትርጓሜውስ ምንድነው?

ቡሄ ማለት (መላጣ ገላጣ) ማለት ነው። በሃገራችን የክረምቱ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በዚሁ በአል አከባቢ ስለሆም ይመስላል  ‘ቡሄ (መላጣ ገላጣ)’ የሚለው ስያሜ የተሰጠው ።

ለቡሄ ጅራፍ የሚጮህበት ምክንያት?

የጅራፉ መጮህ የድምጸ መለኮት፤ጅራፉ ሲጮህ ማስደንገጡ የሃዋርያትን (ጴጥሮስን፣የያእቆብንና፣ የዮሃንስን) ድምጸ መልኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል

ችቦ የሚበራበት ምክንያት?

የቡሄ እለት ማታ ችቦ ያበራል። ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው።  

ዋቢ መጽሃፍትና የበይነ መርብ አድራሻዎች፦

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ፣ “የበዓላትና ዓጽዋማት ቀኖና” ፤ http://ethiopianorthodox.org/amharic/abeyetbealat/yebealatenaatsewamat.pdf

https://am.wikipedia.org/wiki/ደብረ_ታቦር_(ዓመት_በዓል)

Ethiopia

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *