
የመስቀል በአል መልካም ምኞት መግለጫ መልክቶችመልክቶች፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ መልክቶች መልክቶች(sms)
Table of Contents
የመስቀል በአል የሚከበርበት ታሪካዊ መነሻ እና ምክንያት?
የመስቀል በአል
ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ህሙማን መስቀሉን እየዳሰሱ በመስቀሉ እየታሹ ይፈወሱ ስለነበር። በዚህም ተአምራት እየተሳቡ ብዙዎቹ ክርስቲያን ሆኑ። ይህንን ያዩ አይሁዶች መስቀሉን በአንድ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጣሉት።
በየቀኑ የአከባቢው ኗሪ ሁሉ ቆሻሻ ስለሚጥልበት ያ ቦታ እንደ ጉብታ ሆነ።
ነገር ግን ምንም እንኳን ቦታውን ቆፍረው መስቀሉን ለማውጣት ባይችሉም ክርስቲያኖቹ ያንን ቦታ ያውቁት ነበር። በኋላ ግን በጥጦስ ወረራ ክርስቲያኖች ኢየሩሳሌምን ጨርሰው ለቀው ስለወጡ የከተማዋ መልክ ፈጽሞ ስለተለወጠ መስቀሉ የተቀበረበት ቦታ ወዴት እንደሆን ለማወቅ አልተቻለም።
በዚህም ምክኒያት ከ 300 አመት በላይ ከመሬት ውስጥ ተቀብሮ ቆይቷል።
በኋላ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት እሌኒ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች። እዚያም ደርሳ ጉብታ የሆነውን ሁሉ ብታስቆፍር መስቀሉ ያለበትን አላገኘችውም ሰውም ብትጠይቅ መስቀሉ በየት አካባቢ ተቀብሮ እንዳለ የሚጠቁማት አላገኘችም።
በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሄር ፍቃድ ነበርና አንድ አረጋዊ ስሙ ኪርያኮስ የሚባል (ኪራኮስ-ደጎ) የእሌኒን መቸገር አይቶ እንደሚከተለው ይመክራታል “አንቺም ከምረሽ እጣን አፍሺበት በእሳትም አያይዢው የእጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን አይተሽ አስቆፍሪው በዚህ ምልክት ታገኚዋለሽ አላት እሷም ያላትን ሁሉ አደረገች። “
ዘዕጣን አንጸረ ሰገደ ጢስ ድጎ” የእጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደታች ሲመለስ መስቀሉ ያለበትን ቦታ በጣት ጠቅሶ እንደማሳየት ያህል አሳየ ያን ምልክት ይዛ አውጥታለች። “በጎልጎታ ዘደፈኑ አይሁድ ዮመ ተረከበ ዕጸ መስቀል” (ድጎ) ይህን በአል በምላው አለም ያሉ ክርስቲያኖች ያከብሩታል።
በኢትዮጵያ የመስቀል በአል የሚከበረው መቼ ነው?
በኢትዮጵያ የመስቀል ክብረ በአል በየአመቱ መስከረም 17 ቀን በታላቅ ድምቀት የከበራል።
የመስቀል አከባበር ምን ይመስላል?
በመስከረም 16 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮችና ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች የተለያየ እምነትና ቋንቋ ያላቸው። በየከተማው መስቀል አደባባይ በመውጣት በመጀመሪያ የሃይማኖት ስር አቱና ትምህርቱ ከተሰጠ በኋላ ካህናቱም በደመራው ፊት ለፊት ጸሎት አድርሰው
“መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሰርገወ ሰማየ እምኩሉሰ ጸሃየ አርአየ” እያሉ ደመራውን ይዞራሉ።
በመጨረሻም ደመራው ይለኮሳል።
ደመራው በርቶ ሲያልቅ የሚቀረውን ከሰል የእምነቱ ተከታዮች በጣቶቻቸው እየነኩ በግምባራቸው ላይ የመስቀል ምልክት ይሰራሉ።
ማህበረሰቡ ደግሞ የጋራ የሆነውን በአል በመስቀል አደባባይ አክብሮ ከተመለሰ በኋላ በየቤቱ ችቦውን ያበራል።
ልጆች
መስቀል አበራ
አበራ
መስቀሉ
ለኛ አበራ
እያሉ ሆያ ሆዬ ይላሉ።
ሰለመስቀል በአል ሲወራ ሰለጉራጌ እና ወላይታ ሳያነሱ ማለፍ አይቻልም
በኢትዮጵያ ውስጥ መስቀል በተለየ መልኩ በታላቅ ደምቀት ደግሞ በግራጌ እና በ ወላይታ ዞን ውስጥ ይከበራል።
በወላይታ የመስቀል በአል ጊፋታ ተብሎ ይታወቃል።
ክትፎ በሚጥሚጣና በ ብዙ የተነጠረ ቅቤ የተለወሰ በደቃቁ የተከተፈ ቀይ ስጋ ነው።
ክትፎ የሚቀርበው ከሸክላ በተሰራ ጎድጓዳ ሳህን ወይንም
በኮባ ቅጠል ላይ ነው።
በነዚህ አከባቢዎች በመስቀል ወቅት ክትፎ ነው በብዛት የሚበላው በቀንድ ማንኪያ ወይንም ከቆጮ ከሚሰራ ቂጣ ጋር ነው።
ከክትፎው ጎን ደግሞ በተለያዩ ቀመማቀመሞች በሚጥሚጣና በቅቤ የተላወሰ አይብ እና በቅቤ የተሰራ ጎመን አይጠፋም።
የጉራጌ ክትፎ አቤት መጣፈጡ።
በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የመስቀል በአል ከሌሎች የክልል ከተሞች በተለየ በርካታ ህዝብ በተሰበሰበበት በ መስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በአዲስ አበባ በተለይም በርካታ የ ሃገር ውስጥና ከተለያዮ የአለም ሃገራት የመጡ የውጭ ቱሪስቶች ታዳሚ ለመሆን በመዲናዋ ይገኛሉ።
የመስቀል በአል በ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት(UNESCO) በማይዳሰሱ ቅርሶች ምድብ የተካተተ በአል ነው።
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሰህ/ሽ/ዎ/አችሁ። በአሉ የፍቅር፣የጤና፣ የሰላም፣የአንድነት፣የመተባበር፣የመተሳሰብ ይሁንልን።
ሞቅ ያለ ምርጥ በአል እመኝላችኋለው። መልካም የመስቀል በአል ይሁንላችሁ።
ተጨማሪ ድህረ ገጾች