ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)
ኮሮና ቫይረስ
በተቻለ መጠን ከቤትዎ አይውጡ። በተለያየ ምክንያት ከቤት መውጣት ግድ ከሆነብዎት ግን ሁልጊዜም የፊት ጭምብል ይጠቀሙ። ከሰዎች ጋር ያልዎትን ርቀትም ይጠብቁ። እጅዎን በየግዜው በቻሉት መጠን ይታጠቡ።በተጨማሪም በየጊዜው ከአልኮል በተሰሩ የእጅ ማጽጃዎች እጅዎትን ያጽዱ።
የተመጣጠነ ምግብ ይመገቡ።የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ያድርጉ፣ በቂ እንቅልፍም ያግኙ። እነዚህን በማድረግ በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምሩ።
ይህ ክፉ ወቅት ስለራሳችን ደህንነት ብቻ የምንጨነበት ብቻ እንዳይሆን።ድሮም በደማችን የነበረ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነውና የሌላቸውን እና አቅመ ደካሞችን ካለን እያካፈልን እንርዳቸው።
እራስዎንና በተሰብዎን ከኮሮና ቫይረስ ይጠብቁ!
ፈጣሪ ለሁላችንም ምህረት እንዲያድርግልንና ይህን አስከፊ ጊዜ በብርታት የምንወጣበትን ብርታት እንዲሰጠን መልካም ፍቃዱ ይሁን።
ደግሞ እንደ ፈጣሪ ፍቃድ ይህም ቀን ያልፋል!
ለበለጠ መረጃ ይሄንን ድህረ ገጽ ይጎብኙ https://www.healthline.com/coronavirus
ከስር ደግሞ አለም አቀፋዊ የቫይረሱን ስርጭት የሚያሳይ ሰንጠረዥ በጤና ይቆዩ
[ce_corona]