የአዲስ አመት(እንቁጣጣሽ) የእንኳን አደረሳቹ መልካም ምኞት መግለጫ መልክቶች፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ…
እንቁጣጣሽ
ይህ አዲስ ዓመት ብዙ ደስታን እና ሃሴት ያምጣልዎት። ሰላም ፣ ፍቅር እና ስኬት ይስጥዎ ፡፡ መልካም አዲስ አመት።አዲሱ ዓመት የህይወትዎ ምርጥ ዓመት እንደሚሆን ተስፋ አደርጋለሁ ፡፡ ሁሉም ሕልሞችዎ ሁሉ ይፈጸሙ እና ሁሉም ተስፋዎችዎ ይፈጸሙ!
አዲሱን ዓመት የደስታ ፣ የሰላም እና የብልጽግና ያድርግልህ/ሽ/ዎ።
ይህ አዲስ ዓመት በሕይወትዎ ላይ አዲስ ደስታን ፣ አዲስ ግቦችን ፣ አዲስ ስኬቶችን ያምጣ ፡፡ በደስታ የተሞላ አዲስ ዓመት ይሁንልህ/ሽ/ዎ።
እንደ ዓይኖችህ/ሽ ብሩህ ፣ እንደ ፈገግታህ/ሽ ጣፋጭ እና ግንኙነታችንም አስደሳች የሆነ አዲስ ዓመት እንዲሆንልህ/ሽ እመኛለው ፡፡ መልካም አዲስ ዓመት!
በጣም መልካም አዲስ ዓመት እመኛለሁ ፡፡
ሁሉንም የጨለማ ሰዓታት ለማሸነፍ በደስታ እና ጥንካሬ የተሞላ አንድ ዓመት እንዲኖሮት እፈልጋለሁ ፡፡ እውነተኛ በረከት ናችሁ ፡፡ መልካም አዲስ ዓመት ፣ ፍቅር።
አሮጌውን አመት ደህና ሁን ብለን አዲሱን አመት በአዲስ መንፈስና በአዲስ ጉልበት እንቀበለው በደስታ የተሞላ አዲስ አመት ይሁንልን።
እንቁጣጣሽ 2013
አዲስ ዓመት
አዲስ ብርታት
አዲስ ጉልበት
አዲስ መንፈስ
ብሩህ ተስፋ
ሰናይ ዘመን
ሞቅ ያለ መልካም አዲስ አመት እመኝልሃ/ሻ/ለው(ይሁንልን)
2013
አዲስ ብርታት
አዲስ ጉልበት
አዲስ መንፈስ
የየጤና፣የፍቅር፣የይቅርታ፣የአንድነት እና የብልጽና በስራችን ጠንክረን በሃብት የምንትረፈርፍበት ሃግራችንን ወድ ታላቅ ደርጃ ከፍ የምናድርግበት አመት ይሁንልን
የአዲሱ ዓመት 13ቱም ወራቶች በአዳዲስ ስኬቶች የተሞሉ ይሁኑ። ለአንተ/ቺ(ለእርስዎ) እና ለቤተሰቦችህ/ሽ/ብዎ በሃሴት የተሞላ፤ በበረከት የተትረፈረፈ አዲስ አመት እመኝላችኋለው!
አዲስ አመት ፳፻፲፫
የአዲሱ ዓመት ደስታ በሕይወትህ/ሽ/ዎ ውስጥ ለዘላለም እንዲኖር ይሁን። ይሰብከ/ሽው(ያሰቡት) ሁሉ የሚሳካበት የተመኘኅ/ሽውን(የተመኙትን) ሁሉ የምታገኝ/ኚ/በት(የሚያገኙበት) ይሁን ፡፡ መልካም አዲስ ዓመት ፳፻፲፫!
አዲስ ዓመት
365 ባዶ ግጾች
ህይወትህ/ሽ/ዎን በአዲስ ሁኔታ ለመጻፍ አዲስ እድል
ብእሩ በእጅህ/ሽ/ዎ ነው።
፳፻፲፫
መልካም አዲስ አመት።
እንኳን አደረሰን።
‘’ኢትዮጵያ” የሚለው ስያሜ አመጣጥና ትርጓሜው
Table of Contents
‘’ኢትዮጵያ” የሚለው ስያሜ አመጣጥና ትርጓሜው
ኢትዮጵያ የሚለው ቃል መሰረቱ ‘’እንቆጳዝዮን” የሚለው ጥንታዊ የሳባ ቋንቋ ሲሆን በጊዜ ሂደት የሳባ ቋንቋ እየተተወ የግእዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ በስፋት መነገር ሲጀምር ‘’ኢትዮጵግዮን’’ ተባለ ትርጎሙም ኢት ስጦታ፣ ዮጵ ቢጫ ወርቅ፣እንቁ ግዮን ፈሳሽ ወንዝ በአንድ ላይ ‘’የግዮን ወርቅ ስጦታ’’ የሚል ትርጓሜ የሚሰጥ ነው።
የኢትዮጵያ መጠሪያ ስም በተለያየ ጥንታዊ የነገስታት ዘመን የተለያየ ነበረ። ሰለዚህም በመጀመሪያ የኖህ የልጅ ልጅ በሆነው በ’’ኩሽ’’(የካም ልጅ) ስም ኩሽ ተብላ ትጠራ ነበር።
ቀጥሎ በናምሩድ ልጅ(የኩሽ የልጅ ልጅ) ‘’አቢስ’’ ‘አቢስኒያ’ ትባል ነበር።
ከዚያም በሳባኖባ ዘመን ‘’ኑብያ’’ ትባልም ነበር በዚህም ሳባኖባ የተባለውም በኖህ ዘር ውስጥ ሁለት ሳባ ሰለነበረ ነው 1ኛው የኖህ የልጅ ልጅ ኩሽ(የካም ልጅ) የወለደው ሳባ ነው ይህን ከሌላው ለመለየት ሳባ 1ኛ ወይም ሳባኖባ ይሉታል።
2ኛው ደግሞ የካም ወንድም የሴም የዘር ግንድ የሆነው የዮቅጣን ልጅ ሳባ ነው ይህን ደግሞ ሳባ 2ተኛ ወይም ‘’ሳባሻባ’’ ይሉታል ።
ከዚያም ከሴም ዘሮች ውስጥ ነገደ አጋዝያን ወደ ኢትዮጵያ ከመጡ በኋላ ደግሞ ከእነሱ አንዱ በሆነው በኢትዮጲስ 1ኛ ዘመነ መንግስት…. ኢትዮጵያ ተብላ ተሰየመች ።
እንደገና በየጊዜው ወደ ኢትዮጵያ በገቡት ነገደ ‘’ሃበሳ’’ን (በዛሬ ምእራብ የመን አከባቢ የሚገኙ በጥንት ጊዜ ከሃገራቸው ወደ ሰሜን ኢትዮጵያ የመጡ) ጊዜ ደግሞ በሳባውያን ፈደል ‘ሳ’ የነበረው በአረብኛ ‘ሳ’ ፈደል በ ‘ሻ’ ፈደል ተለውጣ ‘ሃበሻ’ የሚለው ስም እንደመጣ ይታመናል።
ሆኖም ግን ሃበሻ የሚለው ቃል በኢትዮጵያ በስፋት እየታወቀ የመጣው ቆይቶ በአክሱም ዘመነ መንግስት ነው። በአፍሪካ ቀንድ የመጀመሪያው ሃበሻ የሚለው ቃል ተጽፎ የተገኘው በ 4ተኛው መቶ ክፍለዘመን በንጉስ ኢዛና የንግስና ጊዜ ነው።
ፑንት፣ኑቢያ፣የሃበሻ ግዛት፣ አቢሲኒያ፣ኩሽ እነዚህ ሁሉ በተለያዩ መጽሃፋት ላይ ኢትዮጵያዊያንንና የኢትዮጵያን ግዛት የሚገልጹ ናቸው።
የኢትዮጵያ የመጀመሪያው መጠሪያ ስም፣መሰረቱ፣ምንጩ የቱ ነው?
ኢትዮጵያ በየለያዩ ጸሃፍት ዘንድ በተለያየ አጠራርና ስም ስትጠራ መኖሯ እንዳለ ሆኖ በዋናነት በኦሪት ላይ ‘’ኩሽ‘’ ተብላ ስፍራ እናገኛለን።
ከዚህ በኋላ 70 ሊቃውንት በጋራ ሆነው ብሉይን ከእብራይስጥ ወደ ጽርዕ/ግሪክ/ ሰተረጉሙ ‘’ኩሽ‘’ የሚለውን ቃል/ከግብጽ በስተደቡብ ያለውን አገር ሁሉ ለመጠቆም ይጠቀሙበት የነበረውን የነገድ አባት ስም/ ‘’ አይቶ ፒያ’’ ወይም ‘’Aithio – Pia’’ ብለው ቅ.ል.ክ 282 ላይ ተረጎሙት።
ይህንኑ ወደ ግእዝ ሲተረጉሙት ቃሉን ብቻ እንደወረደ ‘’ ኢትዮጵያ’’ ብለው አሰፈሩትና ከግእዝ ወደ አማርኛ ሲተረጎምም እንደገና ያለፍቺ ሆሄውን ብቻ በመውሰድ ሃገሯን ‘’ኢትዮጵያ’’፤ ህዝቡን ‘’ ኢትዮጵያዊ’’ አሉት።
ይህንንም ተመርኩዘው በርካታ የታሪክ ጸሃፍት ኢትዮጵያ የሚለው ቃል መሰረት ግሪክ ነው ትርጓሜውም ‘’ በጸሃይ የጠቆረ፣ በጸሃይ የተቃጠለ ፊት ያላቸው።’’ ብለው የውስዱታል። ይህም ከላይ እንዳየነው Aithio – Pia’’ ተብሎ ቅ.ል.ክ 282 ከተተረጎመው ትርጓሜ ላይ ‘’ አይቶ’’ ጥቁር፣ አቃጠለ የሚል ትርጉም ሲሰጥ ‘’ኦፕያ’’ ወይም ‘’ኦጵስ’’ ፊት የሚል ትርጓሜ ይሰጣል።
ይህ ትርጓሜ ልክ እንዳልሆነ የሚያሳየን የተለያዩ ማመሳከሪያዎች?
ራሱ የግሪክ ተወላጅ የሆነው ታላቁ ሆሜር በጻፈው እጅግ ተደናቂ በሆነው ኤልያድ/lliad/ እና ኦድሰይ(odyssey) ላይ
የአማልክት አባት ዜውስ ሃያላኑን ኢትዮጵያዊያንን ለማየትና አብሯቸው ምግብ ለመብላት ወደ ታላቁ ወንዝ ይወርዳል..። እያለ የተረከው ቅ.ል.ክ ከ1000 – 900 ባለው ጊዜ መካከል ነበር።
የኋለኛው ዘመን ግሪካዊ ሊቅ ሄሮደተስም ቅ.ል.ክ 490 ላይ የተወለደው
ስለዚህ በአጠቃላይ ኢትዮጵያ የሚለው ቃል ከግሪክ የመጣ ላለመሆኑ ‘’ኢትዮጲስ 1ኛ’’ እና ‘’ኢትዮጲስ 2ኛ” የሚለው የነግስታት መጠሪያ ስም በቅደም ተከተል ከክርስቶስ ልደት በፊት 1856 – 1800 እና 1730 – 1700 በኢትዮጵያ የነገሱ ነግስታት በመሆኑ 70 ሊቃውንት የተረጎሙት መጽሃፍ ማለትም ኩሽ የሚለውን ወደ ግሪክ‘’ አይቶ ፒያ’’ በለው የተረጎሙትን ግን ከክርስቶስ በፊት 282 ላይ መሆኑ ኢትዮጵያ ከግሪክ የመጣ ነው የሚለውን ውድቅ ያደርገዋል።
እነ ንጉስ ኢትዮጲስ የአጋዚያን የነገስታት ዝርዝር ውስጥ ያሉ ናቸው የግእዝ ቋንቋ ደግሞ በአጋዝያን ዘመን ነበረ ፤ በግዕዝ የተጻፈ ሰነድም ሞልቷል። የአሃዝ ቁጥርም ነበራቸው፤ ኢትዮጵያ የሚለውም ቃል በግሪኮች ሳይታወቅ በፊት በኢትዮጵያ ነበረ ራሱን የቻለ ትርጉምም ነበረው።
‘’ኢት ስጦታ ፣ ዮጵ ቢጫ ወርቅ ወይም እንቁ ፣ ግዮን ፈሳሽ ወንዝ፣ በጥቅል ኢትዮጵግዮን ‘የግዮን ወርቅ ስጦታ ተብሎ በሱባ/በሳባ/ ይተረጎማል’’ /መጽሃፈ አብርሂት መሪ ራስ አማን በላይ 1999 አ.ም/
ኢትዮጵያ ማለት በአሁኑ አገላለጽ ‘’ኢት ዮጵ’’ያ የአማርኛ አባት በሆነው ግእዝ ‘’ኢትዮጳግዮን‘’
ቋንቋ ከመከፋፈሉ በፊት በኖህና በቤተሰቦቹ ዘመን ኩሽቲክ ሴሜቲክ ተብሎ ከመከፋፈሉ በፊት በነበረው የግእዝ አባት በሆነው በሳባ ቋንቋ በነበራት ስያሜ ‘’እንቆጳዝዮን‘’ የተባለች ሃገር ናት ።
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች
‘’ኢትዮጵያ” የሚለው ስያሜ አመጣጥና ትርጓሜው
ኢትዮጵያ የሚለው ቃል መሰረቱ ‘’እንቆጳዝዮን” የሚለው ጥንታዊ የሳባ ቋንቋ ሲሆን በጊዜ ሂደት የሳባ ቋንቋ እየተተወ የግእዝ ቋንቋ በኢትዮጵያ በስፋት መነገር ሲጀምር ‘’ኢትዮጵግዮን’’ ተባለ ትርጎሙም ኢት ስጦታ፣ ዮጵ ቢጫ ወርቅ፣እንቁ ግዮን ፈሳሽ ወንዝ በአንድ ላይ ‘’የግዮን ወርቅ ስጦታ’’ የሚል ትርጓሜ የሚሰጥ ነው።
ኢትዮጵያ ማለት በጸሃይ የጠቆረ፣ በጸሃይ የተቃጠለ ፊት ያላቸው ማለት ነው ?
አይደለም ምክንያቱም ራሱ የግሪክ ተወላጅ የሆነው ታላቁ ሆሜር በጻፈው እጅግ ተደናቂ በሆነው ኤልያድ/lliad/ እና ኦድሰይ(odyssey) ላይ
‘’ በኢትዮጵያ የሚኖሩ ህዝቦች እጅግ ሃያላን እጅግ የሚያምሩና የተከበሩ ናቸው..’’ ይላል፤ መዝሙር ቁጥር 423 ላይ።
የአማልክት አባት ዜውስ ሃያላኑን ኢትዮጵያዊያንን ለማየትና አብሯቸው ምግብ ለመብላት ወደ ታላቁ ወንዝ ይወርዳል..። እያለ የተረከው ቅ.ል.ክ ከ1000 – 900 ባለው ጊዜ መካከል ነበር።
ዋቢ መጽሃፍትና ድህረ ገጾች
ፍስሃ ያዜ ካሳ። (2003 አ.ም)። የኢትዮጵያ የ5 ሺ አመት ታሪክ ከኖህ እስከ ኢህአዴግ መጽሃፍ 1። አዲስ አበባ፣ አልፋ አሳታሚዎች።
መሪ ራስ አማን። (1999 አ.ም)። መጽሓፈ አብርሂት።አዲስ አበባ፣
Homer. The Iliad with an English Translation by A.T. Murray, Ph.D. in two volumes. Cambridge, MA., Harvard University Press; London, William Heinemann, Ltd. 1924.
https://journals.bdu.edu.et/index.php/ejss/article/view/69/125
The Odyssey. Fagles, R.. New York,Viking., Penguin Books.1997.
https://department.monm.edu/classics/courses/clas240/Africa/homeronethiopians.htm
Herodotus, with an English translation by A. D. Godley. Cambridge. Harvard University Press. 1920.
http://www.perseus.tufts.edu/hopper/text?doc=Perseus%3Atext%3A1999.01.0126%3Abook%3D3&force=y
የኢሬቻ በአል መልካም ምኞት መግለጫ መልክቶች፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ መልክቶች መልክቶች…
Table of Contents
የኢሬቻ በአል
የኢሬቻ በአል በኢትዮጵያ በኦሮሞ ብሄር በገዳ ስርአት ለ ዋቃ (waaqa) ምስጋና ለማቅረብና ጸሎት ለማድረስ የሚከናወን በአል ነው።
የገዳ ስርአት ፍትሃዊ የሆነ ማህበራዊ ፣ፖለቲካዊ እና ኢኮኖሚያዊ ክስተቶችን በፍትሃዊነትና በእኩልነት ለማስተዳደር የሚረዳ የኦሮሞ ብሄር ትልቅ ተቋም ነው።
የገዳ ስርአት በስሩ irreechaa(ኢሬቻ)፣ ateetee(አቴቴ)፣ siiqqee(ሲቄ)፣ guddifachaa(ጉዲፈቻ)፣harmahoosisu (ሃርማሆሲሱ)፣moggaasa(ሞጋሳ)፣ jaarsummaa (ጃርሱማ) ተቋማትን ይይዛል።
የኢሬቻ በአል መከበር ምክንያት?
የኢሬቻ በአል የሚከበረው በ በጋ ውቅት ሲሆን ለሰው ልጅ እና ለሌሎች ፍጥረታት ሁሉ አስፈላጊ የሆኑ ነገሮችን በሙሉ ለሚያሟላው ዋቃ (ፈጣሪ እንደማለት ነው።) ምስጋናን መግለጫ በአል ነው።
በገዳ ስርአት ዋቃ ሁሉን የፈጠረ የህይወት ምንጭ ነው ተብሎ ስለሚታሰብ ነው። ዋቃ ፍጹም እውነተኛ፣ ንጹህ፣ ሃ ጢያት የሌለበት በአንድ ጊዜ በሁሉም ቦታ መገኘት የሚችል ነው።
በኢሬቻ በአል ወቅት የበአሉ ታዳሚዎች ዋቃን ሰላምና መረጋጋት እንዲያሰፍን፣ህግና ማህበራዊ ስርአት እንዲከበር፣ ተፈጥሮን እንዲጠብቅ እና ብልጽግና እና መትረፍረፍ እንዲመጣ ይለምኑታል።
የኢሬቻ በአል የት ይከበራል?
ኢትዮጵያ ውስጥ
የኢሬቻ በአል የሚከበረው በወንዝ ዳርቻ ወይም ደግሞ በተራራ አናት ላይ ነው።
የኢሬቻ በአል በየአመቱ በመስከረም ወር የመስቀል በአልን ተከትሎ በእሁድ ቀን በ ሆራ ሃርሰዲ( hora harsadi) መሬት በቢሾፍቱ ከተማ በድምቀት ይከበራል። ለሁለተኛ ጊዜ ደግሞ በመጋቢት ወር ይከበራል።
የኢሬቻ በአል በዋነኝነት በቢሾፍቱ ከተማ ይከበር እንጂ በሌሎች ቦታዎች ማለትም በ መልካ አቴቴ(malkaa ateetee)(ወደ ቡራዩ ከተማ አካባቢ፣በገፈርሳ ወንዝ ዙሪያ) ፣በቱሉ እንጅሮ(ireechaa tulluu injirroo)(ምስራቅ ወለጋ ) ይከበራል።
የአቴቴ እና ሲቄ ተቋማት በአል
ሰለኢሬቻ በአል ሲወራ የአቴቴ(ateetee) እና የሲቄ(siiqqee) ተቋማት በአል ሳይታወስ አይታለፍም። እነዚህ በአላት በተለይም የሴቶች በአላት ናቸው።
የአቴቴ በአል የወላድነት፣ፍሬ የመስጠት በአል ሲሆን በዚህ በአል በሴቶች የሚመራ የጸሎት፣የምርቃትና የይቅርታ ስነስርአቶች ይከናወናሉ።
አቴቴ በዋነኝነት የሴቶች በአል ሲሆን ከወንዶች ይልቅ ፈጣሪ ለሴቶች ጸሎት በቶሎ ምላሽ ይሰጣል ተብሎ ስለሚታመን በአቴቴ ሴቶች ጸሎታቸውን በተለያየ ጊዜ ለዋቃ ያደርሳሉ።
ሲቄ ደግሞ ሴቶች ጋብቻ በሚፈጽሙበት ጊዜ የሚሰጣቸው በትር ሲሆን ይህም በትር የሴቶችንና የወንዶችን እኩልነት ያሳያል።
የኢሬቻ በአል በ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ ሳይንስ እና ባህላዊ ድርጅት(UNESCO) በማይዳሰሱ ቅርሶች ምድብ የተካተተ በአል ነው።
የመስቀል በአል መልካም ምኞት መግለጫ መልክቶችመልክቶች፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ መልክቶች መልክቶች(sms)
Table of Contents
የመስቀል በአል የሚከበርበት ታሪካዊ መነሻ እና ምክንያት?
የመስቀል በአል
ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሞቶ ከተነሳ በኋላ ህሙማን መስቀሉን እየዳሰሱ በመስቀሉ እየታሹ ይፈወሱ ስለነበር። በዚህም ተአምራት እየተሳቡ ብዙዎቹ ክርስቲያን ሆኑ። ይህንን ያዩ አይሁዶች መስቀሉን በአንድ ቆሻሻ ማጠራቀሚያ ጣሉት።
በየቀኑ የአከባቢው ኗሪ ሁሉ ቆሻሻ ስለሚጥልበት ያ ቦታ እንደ ጉብታ ሆነ።
ነገር ግን ምንም እንኳን ቦታውን ቆፍረው መስቀሉን ለማውጣት ባይችሉም ክርስቲያኖቹ ያንን ቦታ ያውቁት ነበር። በኋላ ግን በጥጦስ ወረራ ክርስቲያኖች ኢየሩሳሌምን ጨርሰው ለቀው ስለወጡ የከተማዋ መልክ ፈጽሞ ስለተለወጠ መስቀሉ የተቀበረበት ቦታ ወዴት እንደሆን ለማወቅ አልተቻለም።
በዚህም ምክኒያት ከ 300 አመት በላይ ከመሬት ውስጥ ተቀብሮ ቆይቷል።
በኋላ በአራተኛው መቶ ክፍለ ዘመን የንጉስ ቆስጠንጢኖስ እናት ንግስት እሌኒ ወደ ኢየሩሳሌም ሄደች። እዚያም ደርሳ ጉብታ የሆነውን ሁሉ ብታስቆፍር መስቀሉ ያለበትን አላገኘችውም ሰውም ብትጠይቅ መስቀሉ በየት አካባቢ ተቀብሮ እንዳለ የሚጠቁማት አላገኘችም።
በመጨረሻ ግን የመስቀሉ መውጣት የእግዚአብሄር ፍቃድ ነበርና አንድ አረጋዊ ስሙ ኪርያኮስ የሚባል (ኪራኮስ-ደጎ) የእሌኒን መቸገር አይቶ እንደሚከተለው ይመክራታል “አንቺም ከምረሽ እጣን አፍሺበት በእሳትም አያይዢው የእጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደ ታች ሲመለስ አቅጣጫውን አይተሽ አስቆፍሪው በዚህ ምልክት ታገኚዋለሽ አላት እሷም ያላትን ሁሉ አደረገች። “
ዘዕጣን አንጸረ ሰገደ ጢስ ድጎ” የእጣኑ ጢስ ወደ ላይ ወጥቶ ወደታች ሲመለስ መስቀሉ ያለበትን ቦታ በጣት ጠቅሶ እንደማሳየት ያህል አሳየ ያን ምልክት ይዛ አውጥታለች። “በጎልጎታ ዘደፈኑ አይሁድ ዮመ ተረከበ ዕጸ መስቀል” (ድጎ) ይህን በአል በምላው አለም ያሉ ክርስቲያኖች ያከብሩታል።
በኢትዮጵያ የመስቀል በአል የሚከበረው መቼ ነው?
በኢትዮጵያ የመስቀል ክብረ በአል በየአመቱ መስከረም 17 ቀን በታላቅ ድምቀት የከበራል።
የመስቀል አከባበር ምን ይመስላል?
በመስከረም 16 በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ተከታዮችና ሌሎች የኢትዮጵያ ህዝቦች የተለያየ እምነትና ቋንቋ ያላቸው። በየከተማው መስቀል አደባባይ በመውጣት በመጀመሪያ የሃይማኖት ስር አቱና ትምህርቱ ከተሰጠ በኋላ ካህናቱም በደመራው ፊት ለፊት ጸሎት አድርሰው
“መስቀል አብርሃ በከዋክብት አሰርገወ ሰማየ እምኩሉሰ ጸሃየ አርአየ” እያሉ ደመራውን ይዞራሉ።
በመጨረሻም ደመራው ይለኮሳል።
ደመራው በርቶ ሲያልቅ የሚቀረውን ከሰል የእምነቱ ተከታዮች በጣቶቻቸው እየነኩ በግምባራቸው ላይ የመስቀል ምልክት ይሰራሉ።
ማህበረሰቡ ደግሞ የጋራ የሆነውን በአል በመስቀል አደባባይ አክብሮ ከተመለሰ በኋላ በየቤቱ ችቦውን ያበራል።
ልጆች
መስቀል አበራ
አበራ
መስቀሉ
ለኛ አበራ
እያሉ ሆያ ሆዬ ይላሉ።
ሰለመስቀል በአል ሲወራ ሰለጉራጌ እና ወላይታ ሳያነሱ ማለፍ አይቻልም
በኢትዮጵያ ውስጥ መስቀል በተለየ መልኩ በታላቅ ደምቀት ደግሞ በግራጌ እና በ ወላይታ ዞን ውስጥ ይከበራል።
በወላይታ የመስቀል በአል ጊፋታ ተብሎ ይታወቃል።
ክትፎ በሚጥሚጣና በ ብዙ የተነጠረ ቅቤ የተለወሰ በደቃቁ የተከተፈ ቀይ ስጋ ነው።
ክትፎ የሚቀርበው ከሸክላ በተሰራ ጎድጓዳ ሳህን ወይንም
በኮባ ቅጠል ላይ ነው።
በነዚህ አከባቢዎች በመስቀል ወቅት ክትፎ ነው በብዛት የሚበላው በቀንድ ማንኪያ ወይንም ከቆጮ ከሚሰራ ቂጣ ጋር ነው።
ከክትፎው ጎን ደግሞ በተለያዩ ቀመማቀመሞች በሚጥሚጣና በቅቤ የተላወሰ አይብ እና በቅቤ የተሰራ ጎመን አይጠፋም።
የጉራጌ ክትፎ አቤት መጣፈጡ።
በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ የመስቀል በአል ከሌሎች የክልል ከተሞች በተለየ በርካታ ህዝብ በተሰበሰበበት በ መስቀል አደባባይ በታላቅ ድምቀት ይከበራል። በአዲስ አበባ በተለይም በርካታ የ ሃገር ውስጥና ከተለያዮ የአለም ሃገራት የመጡ የውጭ ቱሪስቶች ታዳሚ ለመሆን በመዲናዋ ይገኛሉ።
የመስቀል በአል በ የተባበሩት መንግስታት የትምህርት ፣ ሳይንስ እና ባህል ድርጅት(UNESCO) በማይዳሰሱ ቅርሶች ምድብ የተካተተ በአል ነው።
እንኳን ለብርሃነ መስቀሉ በሰላምና በጤና አደረሰህ/ሽ/ዎ/አችሁ። በአሉ የፍቅር፣የጤና፣ የሰላም፣የአንድነት፣የመተባበር፣የመተሳሰብ ይሁንልን።
ሞቅ ያለ ምርጥ በአል እመኝላችኋለው። መልካም የመስቀል በአል ይሁንላችሁ።
ተጨማሪ ድህረ ገጾች
የ ደብረ ታቦር (ቡሄ) የእንኳን አደረሳቹ (መልካም ምኞት መግለጫ)…
Table of Contents
- ቡሄ-በሉ.mp3 (382 downloads ) የ ደብረ ታቦር (ቡሄ) በአል መነሻ
የዚህ በዓል መሠረት የክርስትና እምነት ሲሆን፣ በግእዝ ደብረ ታቦር የታቦር ተራራ ማለት ነው ፡፡ የታቦር ተራራ የሚገኘው አሁን ፍልስጤም ተብሎ በሚጠራው ሀገር ነው፡፡ ደብረ ታቦር ወይንም የታቦር ተራራ ኢየሱስ ክርስቶስ ሦስት ደቀ መዛሙርቱን ይዞ ወደ ተራራው የወጣበትና ፊቱ እንደ ጸሃይ የበራበት ልብሱም እንደብርሃን ነጭ የሆነበት ቦታ ነው፡፡ ይህ ቦታ ጌታ ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት ተራራ ነው።
ይህ በአል በየአመቱ ነሃሴ 13 ቀን በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
የደብረ ታቦር በአል በብዙሃን ዘንድ የሚታወቀው ‘ቡሄ’ የሚባለውን ቅጥያ ስም እንዴት አገኘ ትርጓሜውስ ምንድነው?
ቡሄ ማለት (መላጣ ገላጣ) ማለት ነው። በሃገራችን የክረምቱ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በዚሁ በአል አከባቢ ስለሆም ይመስላል ‘ቡሄ (መላጣ ገላጣ)’ የሚለው ስያሜ የተሰጠው ።
‘ድርጊቱ በተፈጸመበት በፍልስጤም ግን የደመና መልክ የማይታይበት ፍጹም የበጋ ወራት ነው” በሃገራችን ህጻናቱ ይህ በአል ከመድረሱ በፊት ቀደም አድርገው ጅራፍ ሲገምዱና ሲያጮሁ(ሲያናጉ) ይሰነብታሉ። እናቶችም ለዚሁ በአል የሚሆን ዳቦ ለመጋገር (የሚከበረው በዳቦ(ሙልሙል ዳቦ) ነውና) ስንዴአቸውን ሲያጥቡ ሲፈትጉ ይሰነብታሉ።
በአሉ እንደ ነገ ሲሆን እንደ ዛሬ በዋዜማው (ነሃሴ 12) የሰፈር ህጻናት በየቤቱ እየዞሩ “ቡሄ በሉ! ቡሄ መጣ ያ መላጣ ቅቤ ቀቡት እንዳይነጣ። እዚህ ለይ ቡሄ ያሉት ዳቦውን ነው። በዚህ ጊዜ እናቶች ካዘጋጁት ዳቦ እያነሱ ይሰጧቸዋል።ሄደው ዳቦአቸውን እየገመጡ ሲጋረፉ ይውላሉ።
ለቡሄ ጅራፍ የሚጮህበት ምክንያት?
የጅራፉ መጮህ የድምጸ መለኮት፤ጅራፉ ሲጮህ ማስደንገጡ የሃዋርያትን (ጴጥሮስን፣የያእቆብንና፣ የዮሃንስን) ድምጸ መልኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል።
ችቦ የሚበራበት ምክንያት?
የቡሄ እለት ማታ ችቦ ያበራል። ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው። “ የቡሄ እለት ለዘመድ ለአዝማድ ለእያንዳንዱ ቤተሰብ በልጆቹ ልክ ዳቦ ይሰጣል። በተጨማሪም ለክርስትና ልጅ ለሰጡት ልጅ ለአማች፣ ምራት፣ በቅርብ እውቅያ ላለውም ሁሉ የቡሄ ዳቦ ይሰጣል።
በኢትዮጵያ ኦርቶዶድስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ተማሪ ቤት ደሞ ደብረ ታቦር የተማሪዎች በአል ነው። ተማሪዎች ቀደም አርገው (ስለ ደብረ ታቦር) እያሉ እህሉን ጌሾውን ብቅሉን ይለምናሉ፤ ህዝቡም በአሉን ስለሚያውቅ በገፍ ይሰጣቸዋል።
የደብረ ታቦር እለት ጠላውን ጠምቀው ቆሎውን ቆልተው ዳቦውን ጋግረው ሊያስቅድሱ የመጡትን ምእመናን ሁሉ ከቅዳሴ በኋላ ይጋበዛሉ። ይህ እስካሁን በቤተክርስቲያን በትምህርት ቤቶች የሚሰራበት ነባር ትውፊት ነው።
እስቲ ደግሞ በአሁኑ ዘመን ያለውን ዘመናዊ የሆያ ሆዬ ሙዚቃ እነሆ
Hoya-Hoye-_-Assiyo-Bellema-short-version-Westpark-Music-2.mp3 (655 downloads )የዚህን ሙዚቃ ሙሉ ይዘት ለማውረድ ወደዚህ አድራሻ ይሂዱ 👇👇
https://westparkmusic.bandcamp.com/track/hoya-hoye-assiyo-bellema-short-version
መልካም የ ደብረ ታቦር (ቡሄ) በአል ይሁንላችሁ!!
በተደጋጋሚ የሚጠየቁ ጥያቄዎች (FAQ)
የደብረ ታቦር በአል በብዙሃን ዘንድ የሚታወቀው ‘ቡሄ’ የሚባለውን ቅጥያ ስም እንዴት አገኘ ትርጓሜውስ ምንድነው?
ቡሄ ማለት (መላጣ ገላጣ) ማለት ነው። በሃገራችን የክረምቱ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታየው በዚሁ በአል አከባቢ ስለሆም ይመስላል ‘ቡሄ (መላጣ ገላጣ)’ የሚለው ስያሜ የተሰጠው ።
ለቡሄ ጅራፍ የሚጮህበት ምክንያት?
የጅራፉ መጮህ የድምጸ መለኮት፤ጅራፉ ሲጮህ ማስደንገጡ የሃዋርያትን (ጴጥሮስን፣የያእቆብንና፣ የዮሃንስን) ድምጸ መልኮት መደንገጣቸውንና መውደቃቸውን ያስታውሳል
ችቦ የሚበራበት ምክንያት?
የቡሄ እለት ማታ ችቦ ያበራል። ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው።
ዋቢ መጽሃፍትና የበይነ መርብ አድራሻዎች፦
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤ/ክ፣ “የበዓላትና ዓጽዋማት ቀኖና” ፤ http://ethiopianorthodox.org/amharic/abeyetbealat/yebealatenaatsewamat.pdf
የአረፋ (ኢድ አል አድሃ) የእንኳን አደረሳቹ (መልካም ምኞት መግለጫ)…
Table of Contents
የአረፋ በአል አመጣጥ ታሪክ
‹የመሥዋዕት በዓል› በመባልም የሚታወቀው ኢድ አል አድሃ በዓለም ዙሪያ በሚገኙ የእስልምና እምነት ተከታዮች ዘንድ በድምቀት ከሚከበሩት ሁለት የእስልምና በዓላት መካከል አንዱ ነው (ሌላው የኢድ አል ፈጥር ነው) ፡፡
የዚህ ታልቅ በአል መነሻ ምክያት ተብሎ የሚታመነውም አላህ የነቢያት አባት ነብዩ ኢብራሂምን በእርሱ ላይ ያለውን እምነት እና ታዛዥነቱ ለማረጋገጥ ፈትኖት እንደነበረና ነብዩ ኢብራሂምም ታዛዥነቱ ለማሳየት የ13 ዓመት ልጁን እስማኤልን ለመስዋት ማቅረቡ ፡፡ ነገር ግን ፣ አብርሃም ልጁን መስዋእት ከማድረጉ በፊት ፣ አላህ መልአኩን ጅብሪልን በመላክ በልጁ ምትክ በግ መተካቱ ነው ፡፡
ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ሰዎች እንስሳትን በመሰዋት ይህን በዓል ያከብራሉ። በአሉ ከእስልምና ጋር ታላላቅ የእምነት መገለጫዎች አንዱ ነው፡፡ በአሉ በኢትዮጵያ እስልምና ተከታዮች ዘንድም በታላቅ ድምቀት ይከበራል።
የአረፋ (ኢድ አል አድሃ) የእንኳን አደረሳቹ (መልካም ምኞት መግለጫ) መልክቶች
አላህ በዚህ ወቅት ሕይወትህ/ሽ/ዎን በደስታ ፣ ልብህ/ሽ/ዎን በፍቅር ፣ ነፍስህ/ሽ/ዎን በመንፈሳዊነት ፣ አዕምሮህ/ሽ/ዎን በጥበብ እንዲሞላው ምኞቴ ነው ፣ በጣም አስደሳች ኢድ እንዲመኝልዎታለው ፡፡
በዚህ በተከበረው በዓል ላይ ደስታን ፣ ፍቅርን ፣ ሰላምን እና ብልጽግናን ያድርግልን ፡፡ በዚህ አስደሳች የኢድ በዓል እርስዎ እና ለቤተሰብዎ መልካም የአረፋ በአል ኢንዲሆን ተመኘሁላችሁ! ኢድ ሙባረክ!
አላህ ምኞቶችህ/ሽ/ዎን ሁሉ እውን ያድርግ እንዲሁም ፍላጎትህ/ሽ/ዎን ሁሉ ያሟላ ፡፡ ለአንተ/ቺ/ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ በሙሉ መልካም የአረፋ በአል እመኛለሁ። ኢድ ሙባረክ!
የአላህ በረከቶች ዛሬ እና ሁል ጊዜም ከእናንተ ጋር ይሁኑ ፡፡ መልካም የአረፋ በአል ይሁንላችሁ።
የአላህ መለኮታዊ በረከቶች ቤትዎን እና ልብዎን በደስታ መንፈስ ይሞሉ እና ለስኬት አዲስ ዕድሎችን ይክፈቱ። መልካም በአል! ኢድ ሙባረክ!
አላህ ፍጥረቱን እንደሚያጠጣ አስደናቂ የሆኑትን በረከቶችንም በአንተ/ቺ እና በወዳጆችህ/ሽ ላይ ያድርግባቸው ፡፡ኢድ ሙባረክ!
አላህ ሁሌም ይባርክህ/ሽ/ዎ ህልሞችህ/ሽ/ዎ እውን ይሁኑ ፣እና ሁል ጊዜም ከአንተ/ቺ/ከእርስዎ ጋር ይሁን ፡፡ኢድ ሙባረክ!
ኮሮና ቫይረስ (ኮቪድ-19)
ኮሮና ቫይረስ
በተቻለ መጠን ከቤትዎ አይውጡ። በተለያየ ምክንያት ከቤት መውጣት ግድ ከሆነብዎት ግን ሁልጊዜም የፊት ጭምብል ይጠቀሙ። ከሰዎች ጋር ያልዎትን ርቀትም ይጠብቁ። እጅዎን በየግዜው በቻሉት መጠን ይታጠቡ።በተጨማሪም በየጊዜው ከአልኮል በተሰሩ የእጅ ማጽጃዎች እጅዎትን ያጽዱ።
የተመጣጠነ ምግብ ይመገቡ።የአካል ብቃት እንቅስቃሴም ያድርጉ፣ በቂ እንቅልፍም ያግኙ። እነዚህን በማድረግ በሽታ የመከላከል አቅምዎን ይጨምሩ።
ይህ ክፉ ወቅት ስለራሳችን ደህንነት ብቻ የምንጨነበት ብቻ እንዳይሆን።ድሮም በደማችን የነበረ ኢትዮጵያዊ ባህላችን ነውና የሌላቸውን እና አቅመ ደካሞችን ካለን እያካፈልን እንርዳቸው።
እራስዎንና በተሰብዎን ከኮሮና ቫይረስ ይጠብቁ!
ፈጣሪ ለሁላችንም ምህረት እንዲያድርግልንና ይህን አስከፊ ጊዜ በብርታት የምንወጣበትን ብርታት እንዲሰጠን መልካም ፍቃዱ ይሁን።
ደግሞ እንደ ፈጣሪ ፍቃድ ይህም ቀን ያልፋል!
ለበለጠ መረጃ ይሄንን ድህረ ገጽ ይጎብኙ https://www.healthline.com/coronavirus
ከስር ደግሞ አለም አቀፋዊ የቫይረሱን ስርጭት የሚያሳይ ሰንጠረዥ በጤና ይቆዩ
[ce_corona]
የገና መልካም ምኞት መግለጫ መልክቶች(መልካም ገና)፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ መልክቶች መልክቶች…
የምስራች ታላቅ ደስታ እንሆ ዛሬ በዳዊት ከተማ መድኀኒት ርሱም ክርስቶስ
ጌታ የሆነ ተወልዶላችዃልና (ሉቃ: ምዕ 2÷11)እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላምና በጤና አደረሳችሁ መልካም የልደት በዐል ይሁንላችሁ።
ሉቃ: ምዕ 2÷11
ዛሬ እጅግ የተለየች ቀን ነች። ምክንያቱም ከስጦታዎች ሁሉ ፍጹም የሆነ ስጦታ ከፈጣሪ ተሰጥቶናልና::
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሰህ! በብዙ በረከቶች የተትረፈረፈ የገና በአል እመኝልሃለው። በተጨማሪም ብዙ ደስታን እና የበለጠ ፍቅርን እመኛለሁ ፡፡ መልካም ገና።
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሰሽ/ህ! በዚህ ገና እና ዓመቱን በሙሉ ፍቅር፣ሰላም እና ደስታ እመኝልሻ/ሃለው። መልካም ገና!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሰህ/ሽ/ው/ዎ! የገና በዓልህ/ሽ/ዎ በዚህ የደስታ ጊዜ በእውነተኛ ተዓምራት እና ትርጉም የተሞላ ይሁን ፡፡ መልካም የተባረከ የገና በእል እንዲሆን የእግዚአብሄር መልካም ፍቃድ እንዲሆን መልካም ምኞቴ ነው።
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሰህ/ሽ/ዎ! በዚህ ቅዱስ ወቅት ዓለምህ/ሽ/ዎ በሙቀት እና በጥሩ በደስታ እንዲሞላ ምኞቴ ነው። በደስታ የተሞላ የገና በዓል እንዲሆንልህ/ሽ/ዎ እንመኛለው። መልካም ገና!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሰህ/ሽ/ዎ! በዚህ ገና እና ዓመቱን በሙሉ ፍቅር፣ሰላም እና ደስታ እመኝልሃ/ሻ/ዎታ/ለው። እግዚአብሔር ይባርክህ/ሽ/ዎ። መልካም ገና!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሰህ/ሽ/ዎ! በብዙ በረከቶች የተትረፈረፈ የገና በአል እምኝልሃ/ሻ/ዎታ/ለው። በተጨማሪም ብዙ ደስታን እና የበለጠ ፍቅርን እመኛለሁ ፡፡ መልካም ገና።
አንተ/ቺን የፍቅር ጓደኛ ማድረጌ በየቀኑ የገና በዓል እንደሆነ ዕንዲሰማኝ ያረገኛል። ሁሌም እወድሃሃ/ሻሃለው መልካም ገና የኔ ጣፋጭ።
በገና እና ዓመቱን በሙሉ እንደ አንተ/ቺ አይነት ጓደኛ በማግኘቴ በጣም ፈጣርን አመሰግናለሁ ፡፡ መልካም ገና ለምርጥ ጓደኛዬ!
ማሬ! ያንተ/ቺ ወዳጅነት እና ፍቅር ለገና ካገኝኋቸው ስጦታዎች ሁሉ ምርጡ ነው ፡፡ መልካም ገና!
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም እና በጤና አደረሰህ/ሽ! ይህንን ወቅት ልዩ እና የሚገርም የሚያደርጉት እንደ አንተ/ቺ ያሉ ጓደኞች ናቸው። መልካም ገና ላንተ/ቺ እና ለቤተሰቦችህ/ሽ በሙሉ።
እንደ አንተ/ቺ ያለ ቤተሰብ ማግኘት ሊሰጥ ከሚችለው ሁሉ የላቀ የገና ስጦታ ነው። መልካም ገና!
ሰላም ፣ ፍቅር እና ደስታ እንመልሃ/ሻ/አችኋ/ለው። እናም ቤትህ/ሽ/አችሁ በበረከት እንዲሞላ የፈጣሪ መልካም ፍቃድ ይሁን። መልካም የገና በዓል ላንተ/ቺ እና ለቤተሰቦችህ/ሽ በሙሉ።
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰህ/ሽ። መልካም የገና በዓል ላንተ/ቺ እና ለቤተሰቦችህ/ሽ በሙሉ።
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረስዎ! ከእርስዎ ጋር አብሮ መሥራት ደስታን የሚሰጥ ነው። እና ደስ የሚል የገናን በዓል ለእርስዎ እና ለቤተሰብዎ እመኛለው።
መልካም ገና ለሁላችን ይሁን! የስኬት እና የስምምነት ወቅት እነሆ መጣልን።
እንኳን ለብርሃነ ልደቱ በሰላም አደረሰህ/ሽ/ዎ! በዚህ ተወዳጅ እና በጣም አስደሳች ወቅት ፍጹም ድስታ እና ሓሴት እመኝልሃ/ሻ/ዎታ/ለው፡፡ አስደሳች የገና በዓል ይሁልህ/ሽ/ዎ!