ስለዚህ ስፍራ
በዚህ ስፍራ ለልዩ በአላትና ክስተቶች እንዲሁም ለሙስሊም እና ለክርስቲያን በአላት ወቅት በቅርብም በሩቅ ላሉ ለጓደኛዎ፣ለወዳጅ ዘመድዎ የሚልኳቸውን ልዩ ልዩ ኢትዮጵያዊ ምርጥ ምርጥ ትኩስ እና አዳዲስ ለየት ያሉ ልብን ይሚያረኩ ኢትዮጵያዊ ወግ እና ለዛ የተላበሱ የመልካም ምኞት መግለጫ መልክቶችን ፣ጥቅሶች፣አጭር ጽሁፍ መልክቶች እና መልክቶች (SMS) ያገኛሉ።
ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ የኢትዮጵያ ቋንቋዎች የሰላምታ አጠያየቅና መልስ አሰጣጥ ጽሁፎችንም አዘጋጅተንልዎታል።
ለጎብኚዎቻችን አመቺ እንዲሆን መልክቶችን በአይነት በአይነት አርገን በተለያዩ ክፍሎች መድበናቸዋል።
የመልካም ምኞት መልክቶቻችንን በጽሁፍ እንዲሁም ጽሁፍን አስግራሚ ጥራት ካላቸው ምስሎች ጋር አጣምረን አቅርበንልዎታል።
አላማችን ለኢትዮጵያውያን በሙሉ ለልዩ ልዩ በአላትና ክስተቶች የሚሆኑ መልክቶችን ማቅረብ ሲሆን። ሰዎች በባእድ ቋንቋ ከሚላላኩ ይልቅ በሃገር በቀል ቋንቋ እና በኢትዮጵያዊ ወግ፣ባህል እና ለዛ የተጻፉትን በዚህ ስፍራ የሚገኙ ምርጥና የማይረሱ በአል የሚያደምቁ መልክቶችን በ መላላክ የሃገርን ባህል እንዲያስጠብቁና መልክቶችን በመላላክ ለራሳችውም ለወዳጅ ዘመድዎቻቸውም ከፍ ያለ ደስታን እንዲያገኙ ነው።
በዚህ ስፍራ የሚገኙ መልክቶችን የጽሁፎቹን ጽሁፎቹ ለትንሽ ጊዜ በመጫን ከሚመጣው ምርጫ ላይ copy የሚለውን በመጫን ከዛ የስልክዎ ሜሴጅ መላኪያ ላይ በመግባት መልክት የሚጻፍበት ባዶ ቦታን ለትንሽ ጊዜ በመጫን ከሚመጣው ምርጫ ላይ paste የሚለውን በመጫን ለሚፈልጉት ወዳጅ ዘመድዎ መልክት ይላኩ።
የምስል መልክቶችን ደግሞ የሚፈልጉትን የምስል መልክት ለትንሽ ጊዜ በመጫን ከሚመጣው ምርጫ ላይ download የሚለውን በመጫን በስልክዎ ላይ አውርደው በሚፈልጉት ጊዜ ለሚፈልጉት ሰው ይላኩ።
እናንተን ማስደሰት ለኛ ትልቅ ደስታ ይሰጠናል።
ይህን ስፍራ በተለያዩ ማህበራዊ ድህረ ገጾች ለሰዎች በማጋርት ስፍራውን ያስተዋውቁዋችው።
ያልዎትን የትኛውም አስተያየት እና መሻሻል ያለባችውን ነገሮች በመልክት መስጫው በኩል ያድርሱን። ወደዚህ ስፍራ መጥተው ስለጎበኙን እናመስግናለን።